0%

Calgary Emergency Management Agency (CEMA) Community Survey


እንኳን ደህና መጡ! በካልጋሪ የድንገተኛ አደጋ አስተዳደር ኤጀንሲ [Calgary Emergency Management Agency (CEMA)] የማህበረሰብ የዳሰሳ ጥናት ላይ ለመሳተፍ ስለተስማሙ በጣም እናመሰግናለን። CEMA የካልጋሪ ከተማ ኤጀንሲ ነው።

CEMA በካልጋሪ ውስጥ ለድንገተኛ አደጋ ወይም ጥፋት ምን ያህል እንደተዘጋጁ መረዳት ይፈልጋል። እኛ በተለይ አዲስ መጤዎች፣ አዛውንቶች፣ በዘር የተከፋፈሉ ማህበረሰቦች፣ አካል ጉዳተኞች እና የከተማ ተወላጅ ማህበረሰቦች አባላት በካልጋሪ ውስጥ ካሉ ጥፋቶች እና አደጋዎች ጋር በተያያዘ መረጃን እንዴት እንደሚያገኙ እና እንደሚተገብሩ በተለየ ሁኔታ የማወቅ ፍላጎት አለን። ይህ መረጃ በካልጋሪ ውስጥ ለጥፋት ስጋቶች እና አደጋዎች በጣም ተጋላጭ የሆኑትን ፍላጎቶች በተሻለ መልኩ የሚያሟላ አዲስ የድንገተኛ አደጋ ዝግጁነት ፕሮግራም፣ ዝግጁ ካልጋሪ (Ready Calgary)፣ የሚባል ለመገንባት ይጠቅማል።

የዚህ መረጃ መሰብሰብ የመረጃ ነፃነት እና የግላዊነት ህግ ክፍል 33(ሐ) የተፈቀደ ሲሆን የዚህ ህግ የግላዊነት ጥበቃ ድንጋጌዎች ይጠብቀዋል። የዚህን መረጃ ስብስብ ወይም አጠቃቀም በተመለከተ ማንኛውም አይነት ጥያቄ ካለዎት፣ እባክዎ readycalgary@calgary.ca ን ያነጋግሩ።

ለዚህ የዳሰሳ ጥናት ሁሉም ምላሾች ስም-አልባ ናቸው። ከአስር 50 ዶላር የስጦታ ካርዶች ለአንዱ ዕጣ ውስጥ በመሳተፍ እድል ለማግኘት ስምዎን ማስገባት ከፈለጉ፣ በዳሰሳ ጥናቱ መጨረሻ ላይ የግንኙነት መረጃዎን ለማጋራት እድሉ ይኖርዎታል።

ተዘጋጅተዋል?

ከታች ያለውን የ“ጀምር” አዝራር ጠቅ በማድረግ እባክዎ የዳሰሳ ጥናቱን ይጀምሩ።
 
Powered by QuestionPro